ዓመታዊ እና ወርሃዊ መታሰቢያ በዓላት
”በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።”ኢሳ.56:5
“የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው።” ምሳ 10፤7 እግዚአብሄር ለቅዱሳን በቸርነቱ ከሰጣቸውበረከት ለመሳተፍ መታሰቢያቸውን ማድረግ የግድ ነው “እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።”/ማቴ 10፤40-46/ ይላልና ይህም የተባለው በነብያት፣ በጻድቃንና በሌሎችምቅዱሳን ስም መታሰቢያ ማድረግ እንደሚገባ ለመግለጽ ነው።
መታሰቢያ አንድ ሰው ለሀገሩ በስራውመልካም ስራ፡ ላበረከተው አስተዋፅኦበጀግንነቱ ታይቶ በዚህች ኃላፊ ጠፊ ዓለምበስሙ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል ፣መንገድተሰርቶለት ሲዘከር ይኖራል ፡፡ እሱ ሕይወት ባይኖርም ስሙ ህያው ሆኖ ሲወሳ ይቆያል፡፡ሰው ሁሉ እንዲያሲታውሰውም ይደረጋል፡፡የእነዚህ አርበኝነት ምድራዊ ሃላፊ ጠፊ ነው።የቅዱሳን መታሰቢያ ስንለል ግን ፤ጻድቁንለማስታወስ በቅዱሱ ስም የሚገነባውንቤተክርስትያን ፣ የሚከበረውን በአል ነው።ከምድራዊው መታሰቢያ ለየት የሚያደርገውምድራዊ መታሰቢያቸው ከሰው ሳይሆንከሰማያዊ አምላክ ፈቃድ በመሆኑ ሥራው ነው። “ምስጋናና ግርማ ነው፤ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል። ለተአምራቱ መታሰቢያን አደረገ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው።5 ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፤ ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።”መዝ.111:3
ዓበይት በዓላትን እና ንዑስ በዓላትን ሙሉ በሙሉ ሳናካትት በከፊል ዓመታዊ በዓላትን እና ወርሃዊ በዓላትን ስንክሳር እና ገድላትን በማንበብ በጦማራችን አቅርበንሎታል፡፡ ለወደፊትም ስራቸውን በተቻለ እናቀርባለን፡፡
ዓመታዊ በዓላት
መስከረም
መስከረም 1. ቅዱስ ራጉኤል (ርእስ አውደ ዓመት/
መስከረም 2. ቅዱስ ዮሀንስ /አንገቱ የተቆረጠበት ቀን/
መስከረም 10. ፀደኒያ ማርያም
መስከረም 15 ቅዱስ እስጢፋኖስ(የተሾመበት) (ይህ በዓል ከመስቀል በዓል ጋር የሚታሰብ ነው)
መስከረም 17 ቅዱስ እስጢፋኖስ /በዓለ መስቀል/
መስከረም 21. መናገሻ ማርያም ፡ግሼን ማርያም ፡እንጦጦ ማርያም
መስከረም 29. ቅድስት አርሴማ
ጥቅምት
ጥቅምት 5. አቡነ ገብረመንፈስ
ጥቅምት 9. አባ አትናስዮስ(እረፍቱ)
ጥቅምት 12.አባ ዲሜጥሮስ(እረፍቱ)
ጥቅምት 13.አባ ዘካርያስ(እረፍቱ)
ጥቅምት 14. አቡነ አረጋዊ (የተሰወሩበት)፡ በገብረክርስቶስ(እረፍቱ)፡ ኢትዮጰያዊውን ጀንደረባ ያጠመቀውን ዲያቆኑ ፊሊጶስ (እረፍቱ)
ጥቅምት 17. ቅዱስ እስጢፋኖስ(የተሸመበት)
ጥቅምት 20. ዮሐንስ ሐፂር(እረፍቱ)
ጥቅምት 21.ነቢየ እግዚአብሔር ኢዩኤል (እረፍቱ)
ጥቅምት 22. ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (እረፍቱ) ጥቅምት 25 አቡነ ሀቢብ አረፈ
ጥቅምት 27. መድሐኔአለም: አባ መብዓ ፅዮን (እረፍታቸው)
2ጥቅምት 8. ቅዱስ አማኑኤል
ጥቅምት 30. ቅዱስ ማርቆስ /ልደቱ/
ህዳር
ህዳር 6. ቁስቋም ማርያም እመቤታችን ስደቷን ጨርሳ የገባችበት
ህዳር 7. ሕንጻ ቤቱ ለጊዮርጊስ/ አጥንቱ ተሰብስቦ መቃብር ቤት የገባበት/
ህዳር 8. በዓል አርባዕቱ እንስሳ /ክሩቤል ሱራፌል/አባኪሮስ
ህዳር 11. ዕረፍተ ቅድስት ሀና
ህዳር 12. ቅዱስ ሚካኤል፡
ህዳር 13. እግዚአብሔር አብ/የአእላፍ መላእክት ቀን
ህዳር 14. አባ ዳንኤል እረፍቱ
ህዳር 15. ቅዱስ ሚናስ እረፍቱ
ህዳር 18. ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ እረፍቱ ከ12ተ ሐዋርያት አንዱ
ህዳር 21. ፅዮን ማርያም/የእመቤታችን በዓል/
ህዳር 24. ሀያአራቱ ካህናተ ሰማይ /ደብረ ሊባኖስ/
ህዳር 25. ቅዱስ መርቆሪዎስ ሰማዕቱ /እረፍቱ/
ህዳር 26. አቡነ ሀብተማርያም /ደብረሊባኖስ/፡ አባ ኢየሱስ ሞአ(እረፍቱ)
ህዳር 27. አባ ተክለሃዋርያት ፡ ሐዋርው ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት አረፈ
ህዳር 29. ተፈፃሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ(እረፍቱ)
ታህሳስ
ታህሳስ 1.ነቢዩ ኤልያስ የተወለደበት ቀን
ታህሳስ 3. በአታ ለማርያም እመቤታችን በሶስት አመቷ ቤተመቅደስ የገባችበት፡ አቡነ ዜና ማርቂስ(እረፍቱ)
ታህሳስ 4. ሐዋርያው እንድርያስ በሰማዕትነት ያረፈበት
ታህሳስ 6. ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ)
ታህሳስ 12. አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
ታህሳስ 13. ቅዱስ ሩፋኤል
ታህሳስ 15. አባ ጎርጎርዮስ (እረፍቱ) ዘሀገረ አርማንያ
ታህሳስ 19. በዓለ ቅዱስ ገብርኤል
ታህሳስ 22. ብስራተ ገብርኤል /እመቤታችን ክርስቶስን እንደምትወልድ ያበሰረበት/
ታህሳስ 24. አቡነ ተክለሀይማኖት /ልደታቸው/
ታህሳስ 28. ቅዱስ አማኑኤል በዓለ ልደት ለእግዚእነ ገና
ታህሳስ 29. ቅዱስ በዓለ ወለድ /ተዘከረ ልደቱ ለእግዚነ/ገና/
ጥር
ጥር 1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሚ ሰማእት (እረፍቱ)
ጥር 4. ቅዱስ ዮሐንስ /ወንጌላዊ/ወልደ ነጎድጓድ
ጥር 6. ኢየሱስ/ግዝረቱ ለእግዚእነ /እየሱስ ገዳም/ ነቢዩ ኤልያስ የተሰወረበት ቀን
ጥር 7. ቅድስት ሥላሴ
ጥር 11. በዓለ ጥምቀት
ጥር 12. በዓለ ቅዱስ ሚካኤል /ቃና ዘገሊላ/
ጥር 13. ቅዱስ ሩፋኤል /የቃና ዘገሊላ በዓል መታሰብያ/
ጥር 14 አቡነ አረጋዊ
ጥር 15. ቅዱስ ቂርቆስ እየሉጣ
ጥር 18. ቅዱስ ጊዮርጊስ /ዝርዎተ አጽሙ/
ጥር 21. የእመቤታችን በዓለ እረፍት
ጥር 22. ቅዱስ ኡራኤል ቃል ኪዳን የተቀበለበትና የተሸመበት ቀን
ጥር 23. ሐዋርያው ጢሞቲዋስ (እረፍቱ)
ጥር 24. አቡነ ተክለሃይማኖት
ጥር 28. ቅዱስ አማኑኤል ለ5000 ሰዎች ጌታችን ህብስቱን ያበረከተበት
የካቲት
የካቲት 3. አባ ያዕቆብ (እረፍቱ)
የካቲት 8. ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ወደ ምኩራብ የገባበት ቀን(የአረጋዊው የስምዖን ታሪክ ልብ የበሉ)
የካቲት 9. አባ በርሱማ (እረፍቱ)
የካቲት 15. ነቢዩ ዘካርያስ (እረፍቱ)
የካቲት 16. ኪዳነምህረት /እመቤታችን ቃልኪዳን የተቀበለችበት/
የካቲት 20. ቅዱስ ፊልጶስ
የካቲት 23. ቅዱስ ጊዮርጊስ
የካቲት 26. ነቢዩ ሆሴዕ (እረፍቱ)
የካቲት 28. ሮማዊው ቅዱስ ቴዌድሮስ(እረፍቱ)
መጋቢት
መጋቢት 4. ቅዱስ ጊዮርጊስ /ደብረዘይት/
መጋቢት 3. ተዝካረ ልደቱ ለአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
መጋቢት 10. መስቀሉን ንግስት እሌኒ ቆፍሬ ያገኘችበት ቀን መድሀኔአለም
መጋቢት 15. ቅድስት ሳራ(እረፍቷ)
መጋቢት 22. ጥንተ ሆሳእና
መጋቢት 27. ቸሩ መድሃኒአለም (የጌታችን ጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያ)
መጋቢት 29. የበዓለ ወልድ /የጌታችን ጽንሰት/
ሚያዝያ
ሚያዝያ 22. አባ ይስሀቅ(እረፍቱ)
ሚያዝያ 23. የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍት
ሚያዝያ 27. ምስካየ ሕዙናን /ስደተኛው መድሀኒአለም/
ሚያዝያ 30. ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ነው
ግንቦት
ግንቦት 1. ልደታ እመቤታችን የተወለደችበት ቀን ነው
ግንቦት 7. ሊቁ አቡነ አትናቲዎስ (እረፍቱ)
ግንቦት 11. ቅዱስ ያሬድ(የተሰወረበት)
ግንቦት 12. አቡነ ተክለሃይማኖት /አፅማቸው የፈለሰበት /ክርስቶስ ሳምራ
ግንቦት 14. አቡነ አረጋዊ፡ ቅዱስ ገብረክርስቶስ
ግንቦት 17. አባ ኤጲፋንዮስ(እረፍቱ)
ግንቦት 21 . እመቤታችን ማርያም /እመቤታችን በድብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአራት ቀን የታየችበት ነው
ግንቦት 24. ቁስቋም ማርያም /የስደቷ መነሻ/
ግንቦት 28. ቅዱስ አማኑኤል፡ ቅድስት አመተ ክርስቶስ (እረፍቷ)
ሰኔ
ሰኔ 8. ከደረቅ ዓለት ላይ ውሃን ያፈለቀበት ከ33ቱ ከእመቤታችን በዓል አንዱ
ሰኔ 9. ታላቁ ነብይ ሳሙኤል(እረፍቱ)(የሐና ልጅ)
ሰኔ 11.ሰማዕቱ ቅዱስ ገላውድዮስ (እረፍቱ)
ሰኔ 12. ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን ከውሃ ያወጣበት ቀን ነው(አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት)፡ ቅዱስ ላሊበላ(እረፍቱ)
ሰኔ 20.ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን
ሰኔ 21. ጌታችን /የእመቤታችንን ቤት ያነጸበት ቀን ነው፡፡ ግሽን ማርያም በጎልጎታ በጌታችን መቃብር የጸለየችበት
ሰኔ 23.ጠቢቡ ሰሎሞን እረፍቱ
ሰኔ 24. አባ ሙሴ ፀሊም(እረፍቱ)
ሰኔ 25. የዮሴፍ ልጅ ሐዋርው ይሁዳ እረፍቱ
ሰኔ 26. ኢያሱ እረፍቱ
ሰኔ 27. እረፍቱ ለሐናንያ ሐዋርያ
ሰኔ 30. ልደተ ዮሐንስ መጥምቅ
ሐምሌ
ሐምሌ 2. ሐዋርያው ታዴዎስ(እረፍቱ)
ሐምሌ 3. አባ ቄርሎስ(እረፍቱ)
ሐምሌ 4. ነቢዩ ሶፎንያስ እረፍቱ
ሐምሌ 5. ጴጥሮስና ጳውሎስ እረፍታቸው
ሐምሌ 7. አጋእዝተ ዓለም ስላሴ በአብርሃም ቤት፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እረፍቱ
ሐምሌ 8. አባ ኪሮስ
ሐምሌ 10.ሓዋርያው ናትናኤል እረፍቱ
ሐምሌ 15. ኤፍሬም ሶርያዊው እረፍቱ
ሐምሌ 16. ወንጌላዊው ዮሐንስ እረፍቱ
ሐምሌ 18 .የጻድቁ የዮሴፍ ልጅ ሐዋርያው ያዕቆብ እረፍቱ
ሐምሌ 19. በዓለ ቅዱስ ገብርኤል ቂርቆስና እየሉጣን ከእሳት ያዳነበት ቀን ነው/ቁልቢ ገብርኤል/
ሐምሌ 22. ቅዱስ ኡራኤል ፡አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የተቀበሉበት
ሐምሌ 23. ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሐምሌ 26. ቅዱስ ዮሴፍ (እረፍቱ) ፡አቡነ ሀብተማርያም ዘደብረሊባኖስ
ሐምሌ 28.ቅድስት መስቀል ክብራ (እረፍቷ)(የቅዱስ ላሊበላ የትዳሩ አጋር)
ሐምሌ 30.ቅድስት ማርያም ክብራ(እረፍቷ)
ነሐሴ
ነሐሴ 7.ፅንሰታ ለማርያም
ነሐሴ 13. እግዚአብሔር አብ በደብረታቦር ተራራ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱ ለእነ ሙሴና ኤልያስ የገለጸበት ቀን ነው/የቡሄ በዓል/
ነሐሴ 15. ቅድስት እነባመሪና(እረፍቷ)
ነሐሴ 16. ኪዳነምህረት
ነሐሴ 19. አባ መቃርስ የስጋው ፈልሰት
ነሐሴ 21. ጌቴ ሴማኒ ገዳም እመቤታችን (ሰበታ)
ነሐሴ 24. አቡነ ተክለሃይማት እረፍታቸው ፤ክርስቶስ ሳምረ
ነሐሴ 27 ቅዱስ ሱርያል(4 ሊቀ መላእክት)
ነሐሴ 28.አበው አብርሃም ይህሳቅ ያዕቆብ (እረፍታቸው)
ጳጉሜ
ጳጉሜ 2.ሐዋርያው ቲቶ (እረፍቱ)
ጳጉሜ 3. ቅዱስ ሩፋኤል
ጳጉሜ 4.አባ ባይሞን(እረፍቱ)
ወርሃዊ በዓላት
1.
1. ልደታ፣ዮሐንስ ፣ራጉኤል ፣እዮብ ፣ኤልያስ ፣ ሶስና
2.
2. በርቶሎሚዎስ ፣ጴጥሮስ ፣አባ ጉባ ፣መሪና
3.
3. በአታ ማርያም ፣ፋኑኤል ፣ዜና ማርቆስ
4.
4. ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ፣አባ መቃርዎስ፣ አባ አብርሐ
5.
5. ጴጥሮስና ጳውሎስ ፣ገብረ መንፈስ ቅዱስ
6.
6. ቁስቋም ፣ኢየሱስ ፣አርሴማ ቅድስት ፣እያሱ
7.
7. አጋዕዝተ አለም ስላሴ ፣ዲዎስቆሮስ
8.
8. ኪሮስ ፣ማቲዮስ፣ ኪሩቤል አርባእቱ እንስሳ፡ ዘካርያስ
9.
9. ሰልስቱ ምዕት፣ ቶማስ ፣እስትንፋሰ ክርስቶስ ፣አትናትዮስ
10.
10. መስቀለ ክርስቶስ ፣ናትናኤል ሐዋርያ ፣ፀደንያ ማርያም
11.
11. ሐና እና ኢያቄም ፣አቡነ ሐራ
12.
12. ሚካኤል፣ አባ ሳሙኤልና ፣ ናትናኤል ሐዋርያ
13.
13. ፀጋ ኢየሱስ/ ዘርአ ብሩክ/ ፣ሩፋኤል ፣እግዚአብሔር አብ
14.
14. አቡነ አረጋዊ ፣ገብረ ክርስቶስ/ገብረ መርአዊ/ ዘሚካኤል ፣ሙሴ ፀሊም
15.
15. ቂርቆስና እየሉጣ ፣ሚናስ
16.
16. ኪዳነ ምህረት ፣ኤልሳቤጥ
17.
17. እስጢፋኖስ ፣ገሪማ ፣ወለተ ጴጥሮስ ፣አቡነ በትረ ማርያም ፣ ያዕቆብ ወልደ ዘብዲዮስ ፣ሙሴ
18.
18. ማዕቀብ አልፋ ፣ኢዩስጣቲዮስ ፣ፊሊጶስ
19.
19. ገብርኤል ፣ስልስቱ ደቂቅ፣ ይመርሐነ ክርስቶስ
20.
20. ፣ዮሐንስ ሀፂር ፤ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን
21.
21. ቅድስት ድንግል ማርያም
22.
22. ሉቃስ ፣ደቅስዮስ ፣ኡራኤል ፣ ብስራተ ገብርኤል
23.
23. ቅዱስ ማር ጊዮርጊስ
24.
24. ተክለ ሐይማኖት ፣ጎርጎርዮስ ፣24ቱ ካህናተ ሰማይ፣ ክርስረቶስ ሰምራ
25.
25. ቅዱስ መርቆሬዎስ ፣አቡነ ሀቢብ
26.
26. ዮሴፍ፣ ቶማስ ዘህንደኬ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም
27.
27. መድሐኔአለም ፣አቡነ መባዓ ፅዮን ተክለ አልፋማርያም
28.
28. አማኑኤል ፣ .አበው አብርሃም ይህሳቅ ያዕቆብ
29.
29. በዓለ እግዚአብሔር (በዓለወልድ)፣ቅዱስ ላሊበላ ፣ቅድስት አርሴማ
30.
30. ቅዱስ ማርቆስ ፡ ዮሐንስ መጥምቅ
“እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።” ዘሌ 19፤2 በተባለው መሰረት ቅዱስ የሚለው ስያሜበምግባር በቱርፋትለጽኑ የሚታየውን አለም ለለወጡ ከዚህ አለም ደስታ ተድላ ይልቅዘላለማዊውን ለመረጡ ፤በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ እራሳቸውን ለኃላፊው ነገር ላላስገዙ የሚሰጥስያሜ ነው። ስለዚህመ ለቅዱሳን የሚገባውን መታሰቢያ እናደርጋለን “እንግዲህ ምን እላለሁ?
ስለጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና። እነርሱበእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራንእየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳናበተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። /ዕብ 11፤26/ የተባለው በፅናትና በትጋት እግዚአብሔርን ላገለገሉ ቅዱሳን ነው፡፡
አስተያየቶ እንዳይለየን የቅዱሳን አምላክ ከሁሉ ነገር ይጠብቀን፡፡